1.3 ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ የታወቁ በሽታዎች
- የተለያዩ በሽታዎች በሰዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡
- መታመም ማለት የጤና መጉዋደል ማለት ነው ህመም ሲኖር ደግሞ በአካል እና በአእምሮ ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል፡፡
- ሰውነታችንና አእምሮአችን በትክክል ከሰራ ሙሉ ጤነኞች ነን እንባላለን ሁላችንም ደስተኛ ኑሮ መኖር እንፈልጋለን፡፡
- ደስተኛ ኑሮ ለመኖር ደግሞ ጤናችን የተሟዋላ መሆን አለበት፡፡
ተማሪዎች! ጤንነታችን የተሟላ ከሆነ
- ጨዋታ ለመጫወት - የፈለግነውን ስራ ለመስራት
- በአግባቡ ትምህርታችንን ለመማር እንቸላለንበሽታ የውስጥ ወይም የውጭ አካላችንን በመጉዳት የዕለት ተዕለት ተግባሩን በትክክል እነዲያከናውን የሚያደርግ የጤና መታወክ ነው፡፡በሽታ በሁለት ይከፈላል።
እነርሱንም 1) ተላላፊ በሽታና 2) ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ናቸው፡፡
ተላላፊ በሽታ
ተላላፊ በሽታ ከበሽተኛው ሰው ወደ ጤነኛ ሰው በጥቃቅን ተህዋስያን አማካኝነት የሚተላለፍ የበሽታ አይነት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ጉንፋን፣ የሳምባ ነቀርሳ፣ ኮሌራና የመሳሰሉት
ተላላፊ ያልሆነ በሽታ
ይህ የበሽታ አይነት ደግሞ ከበሽተኛው ሰው ወደ ጤነኛ ሰው አይተላለፍም፡፡
ምሳሌ፡- የስኩዋር በሽታ፣ የጨጓዋራ በሽታ፣ የደም ግፊትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ጉንፋን እና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ በሽታ መንሰኤዎችና ስለሚያደርሱት ጉዳት እንመለከታለን፡፡
ጉንፋን
1.የጉንፋን በሽታ የሚመጣው በቫይረስ አማካኝነት ነው፡፡
2. ቫይረሶች በጣም ጥቃቅን በዐይን የማይታዩ ተዋህስያን ናቸው፡፡
3. ጉንፋን የሚዛመተው በአየር ውስጥ ነው፡፡
4. ጉንፋን የያዘው ሰው የተለያዩ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡
ለምሳሌ፡- የራስ ምታት፣ ማስነጠስ፣ አክታ፣ የንፍጥ መዝረክረክ እና የመሳሰሉት ምልክቶች ይታዩበታል፡፡
በሽታው ከበሽተኛው ወደ ጤነኛ ሰው የሚተላለፈው በትንፋሽ፤ የመመገቢያ እቃዎችን በጋራ በመጠቀም፣ አፍንጫ እና አፍን ሳይሸፍኑ በመሳል እና በማስነጠስ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ተማሪዎች! ጉንፋን ከያዘን ልናደርጋቸው ከሚገቡ እርምጃዎች ውስጥ፡-
- በቂ እረፍት መውሰድ ይኖርብናል፡፡
- ፍራፍሬዎችን መመገብ ይኖርብናል፡፡
- ትኩስ መጠጦችን መወሰድ እና
- በሽታው ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ ስንስልና ስናስነጥስ መሃረብ መጠቀም ይኖርብናል፡፡
ኤድስ
- ኤድስ ሌላኛው በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡
- ኤድስ በሽታን የሚያመጣው ቫይረስ ኤች.አይ.ቪ በመባል ይታወቃል፡፡
- እንደ ጉንፋን ሁሉ ኤድስም ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
- በሽታው ከሰው ወደ ሰው የሚተለላለፈው በደም ንኪኪ ነው፡፡
ይህም ሊሆን የሚችለው አንድ ሀኪም አንድን መርፌ ለብዙ ሰው ሲጠቀም፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተጠቀሙበትን ስለታማ ነገሮች ስንጠቀም እና በመድማት ላይ የሚገኙ ሰዎችን ደም በመንካት ነው፡፡በመሆኑም ኤድስን ለመከላከል ማድረግ የሚጠበቅብን፡-
1 በህክምና ወቅት ሀኪሙ አዲስ መርፌ መጠቀሙን ማረጋገጥ
2 ሌላ ሰው የተጠቀመበትን ስለታማ ነገር አለመጠቀም እና3 ከማንኛውም የደም ንኪኪ መራቅ ነው፡፡
አሁን በምሳሌነት ጉንፋን እና ኤድስን ወስደን እንጂ ስለ በሽታ ስትማሩ ብዙ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ በሽታዎች እንዳሉ አትዘንጉ፡፡