ምዕራፍ አንድምግብና የቤተሰብ ደህንነት ተማሪዎች በዚህ ምዕራፍ የምንማረው1.1 ምግብ 1.2 የቤተሰብ ንፅህና1.3 የዕረፍት ጊዜና መዝናኛተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ የሚከተሉትን እውቀቶች ታገኛላችሁ፡፡- ተገቢ የአመጋገብ ልምዶችን- የምግብ ብክለት መንስዔዎችን፤ የሚያስከትላቸውን ችግሮች እና መከላከያ ዘዴዎችን- የቤተሰብ ንጽህና እና የአካባቢ ፅዳት አጠባበቅ ልምዶችን እና በፅዳት ጉድለት የሚመጡ በሽታዎችን - ትርፍ ጊዜና የመዝናኛ ጊዜ ለቤተሰብ ደህንነት የሚኖረው ጠቀሜታ - ጊዜያችንን በአግባቡ በመጠቀም- ኤች አይ ቪ/ኤድስ በራሳችሁ በቤተሰባችሁና በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎች እና ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ፍቅርን ማሳየት 1.1 ምግብሀ. ተገቢ የአመጋገብ ልምዶች• የአመጋገብ ልምድ አንድ ሰው ወይም ህብረተሰብ አዘውትሮ የሚመገበውን የምግብ አይነት የአዘገጃጀት ሂደት እና የአመጋገብ ሁኔታ የሚገልፅ ነው፡፡• የምትመገቧቸው ምግቦች ብዙውን ጊዜ በአራት የምግብ ምድቦች ይከፈላሉ እነሱም፡- 1. አትክልትና ፍራፍሬዎች 2. እህልና ጥራጥሬዎች 3. ሥጋ 4. ወተትና የወተት ውጤቶች ናቸው፡፡ 1. አትክልትና ፍራፍሬዎች ማንጎ፤ ፓፓዬ፤ ጥቅል ጎመን፤ ካሮት፤ ብርቱካን፤ አቮካዶ እነዚህ የምግብ አይነቶች ሰውነትን ከበሽታ ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡2. እህልና ጥራጥሬዎች ስንዴ፤ በቆሎ፤ ባቄላ፤ ማሽላ፤ አተር፤ ጤፍ ተማሪዎች እነዚህ እህልና ጥራጥሬዎች ጉልበትና ሙቀት ይሰጣሉ፡፡3. ሥጋ የዶሮ ስጋ፤ የከብት ስጋ፤ የአሳ ስጋ እነዚህ ሰውነታችንን ለመገንባትና ለመጠገን ይረዳል፡፡4. ወተትና የወተት ውጤቶች ቅቤ፤ ወተት፤ አይብተማሪዎች ከወተት ምን አናገኛለን? ጎበዞች! ከወተት እርጎ፣ ቅቤ፣ አሬራ፣ አይብና አጓት አላችሁ አይደል፡፡ ወተት በውስጡ ብዙ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡በአጠቃላይ ወተት፡- - ለሰውነት ጉልበት ይሰጣል- ከበሽታ ይከላከላል- ጤናማ ዕድገት እንዲኖረን ይረዳል፡፡ተማሪዎች አሁን ደግሞ አንድ ትምህረታዊ ጨዋታ እንጫወታለን፡፡ እኔ ማነኝ? ሀ. ከሎሚ ጋር እመሳሰላለሁ፤ ከሱ ግን ወፈር ያልኩና ጣፋጭ ነኝ።ጎበዞች! ብርቱካን ካላችሁ ትክክል ናችሁ፡፡ ለ. የጥራጥሬ ዘር ስሆን በጣም ትንሽ ነኝ፤በየቤቱ በእንጀራ መልክ እበላለሁ፡፡ ጎበዞች! ጤፍ ካላችሁ መልሱን በትክክል አግኝታችሁታል፡፡ሐ. በመልኬ ነጣ ያልኩና ፈሳሽ ነኝ ሕጻን ሆናችሁ በጡጦና በብርጭቆ ጨምራችሁ ትጠጡኛላችሁ፡፡ በትክክል ተመልሷል ወተት ነኝ፡፡መ. ከእንስሳ እገኛለሁ፤ ሰዎች ጠብሰውኝና በወጥ ውስጥም ጨምረውኝ ይበሉኛል፡፡ ጎበዞች! ስጋ ነኝ ።ለ. የተመጣጠነ ምግብ • የተመጣጠነ ምግብ ማለት መጠኑ በቂ የሆነ፤ የተለያዩ የምግብ ምድቦችን የያዘ ማለት ነው፡፡የተመጣጠነ ምግብ ከአራቱም የምግብ ምድቦች ቅልቅል የተዘጋጀ ነው፡፡1. ከአትክልትና ፍራፍሬ2. ከእህልና ጥራጥሬ3. ከስጋና 4. ከወተት ምድቦችን ያካተተ ማለት ነው፡፡ ሐ. የምግብ ብክለት መንስኤዎች የምግብ ብክለት ምንድነው?የምግብ በአይን በማይታዩ ጥቃቅን ነፍሳት (ጀርሞች) መመረዝ ነው፡፡ መንስኤዎቹም - ምግብን አለማብሰል፤ በደንብ ያለመክደን፤ በንፁህ ስፍራ አለማስቀመጥ፤ አካባቢን አለማፅዳት፤ የምግብ መበከልን ያስከትላል፡፡- በተጨማሪም - ምግብን ክፍት መተው- ምግብ በዝንብ ሲወረር- ምግብ ሲዘጋጅ የንፅህና ጉድለት ካለ- ምግብ የሚቀመጥበት ቦታ ነፍሳት በቀላሉ የሚገቡበት ከሆነ- የምግብ ማዘጋጃ ስፍራና እቃ የንፅህና ጉድለት ቢኖረው - ምግብን የሚያዘገጀው ሰው በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊጠቃና- ምግብ የሚዘጋጅበት ውሃ መበከልመ. የምግብ መመረዝ የሚስከትላቸው ጉዳቶች በምግብና በውሃ ብክለት አማካኝነት ከሚመጡ በሽታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ- ኮሌራ - ተቅማጥ እና- ወስፋት ናቸው1. ኮሌራ- ኮሌራ በምግብና በውሀ ብክለት አማካኝነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡- ኮሌራ ከፍተኛ ተቅማጥና ትውከት ያስከትላል፡፡-አስቸኳይ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡ 2. ተቅማጥ• ተከታታይ ውሃማ ተቅማጥ አለው።• ብዙውን ጊዜ ደምና ንፍጥ መሰል ነገር ከሰገራ ላይ ይታያል፡፡• ከሆድ አካባቢ ከፍተኛ ሕመም አለው፡፡ 3. ወስፋት- የትል ዘር ነው - በወስፋት እነንቁላል የተበከለን አፈር በነካው እጃችን ሳንታጠብ ምግብ ብንበላ እንቁላሉ አንጀት ውሰጥ ገብቶ ወደ ትልቅ ወስፋት ያድጋል፡፡ሠ. የምግብ ብክለትን መከላከልየምግብ ብክለትን በሚከተሉት መንገዶች መከላከል ይቻላል፡፡ሀ. ምግብ ከመንካትና ከማዘጋጀት በፊት በሳሙና እጅን መታጠብ። ለ. ጎጂ ተባዮች እንዳያርፉበት ምግብ መሸፈን። ሐ. የምግብ ማዘጋጃ ቦታን ማፅዳት። መ. የምግብ መሥሪያና ማቅረቢያ ዕቃዎችን በአግባቡ በማጠብ በንፅህና መጠበቅ። ሠ. መጠጥና ምግብን ለማዘጋጀት ንፁህ ውሃ መጠቀም። የተበከለ ምግብ ያልተለመደ ጠረንና ጣዕም እንዲሁም ለዕይታ የተለየ መልክ ሊፈጥር ይችላል፡፡