1.2 የ1000፣ 10,000 እና 100,000 ብዜቶች
እንደምንላቹሁ ተማሪዎች ተማሪዎች ዛሬ የ1000፣ 10,000 እና 100,000 ብዜቶች ልንማማር ተገናኝተናል ዝግጁ ናችሁ ልጆች?
ተማሪዎች በስተቀኝ የሚገግኙ ሦስት ሆሄያቸው ሁሉም ዜሮ የሆኑ ሙሉ ቁጥሮች ሁሉ የ1000 ብዜት ናቸው።ተማሪዎች አንድ ቁጥር በ1000 ማባዛት ማለት ቁጥሩን ፅፎ ከቁጥሩ በስተቀኝ፣ ሦስት ዜሮዎችን መፃፍ ማለት ነው።
ምሳሌ 1 23200 የ1000 ብዜት ነው? ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት? በጣም ጥሩ ተማሪዎች 23200 የ1000 ብዜት አይደለም ። ምክያቱም የ 23200 በስተቀኝ የሚገኙ የመጨረሻው ሦስት ሆሄዎች ሁሉም ዜሮ አይደሉም ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል ማለት ነው ።
ምሳሌ 2 45000 የ1000 ብዜት ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት? በጣም ጥሩ ተማሪዎች 45000 የ1000 ብዜት ነው። ምክንያቱም ሁሉም በስተቀኝ የሚገኙ የመጨረሻ ሦስት ዜሮ በመሆናቸው ነው ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል ማለት ነው ። ተማሪዎች እስከ 1,000,000 ያሉ የ10,000 እና የ100,000 ብዜቶችን እናያለን የአንድ ሙሉ ቁጥር በስተ ቀኝ የሚገኙ አራት ሆሄዎች በሙሉ ዜሮ ከሆኑ፤ ቁጥሩ የ10000 ብዜት ነው።
ምሳሌ 153,000 የ10,000 ብዜት ነው? በጣም ጥሩ ተማሪዎች 53000 የ10000 ብዜት አይደለም ። ምክያቱም የ 53,000 በስተቀኝ የሚገኙ የመጨረሻው አራት ሆሄዎች ሁሉም ዜሮ አይደሉም። ምሳሌ 2760,000 የ10,000 ብዜት ነው? በጣም ጥሩ ተማሪዎች 760,000 የ10,000 ብዜት ነው ። ምክያቱም የ 760,000 በስተቀኝ የሚገኙ የመጨረሻው አራት ሆሄዎች ሁሉም ዜሮ ናቸው። ተማሪዎች በስተቀኝ የሚገኙ አምስት ሆሄዎች በሙሉ ዜሮ ከሆኑ፤ ቁጥሩ የ100,000 ብዜት ነው
ምሳሌ 1400,000 የ100,000 ብዜት ነው? በጣም ጥሩ ተማሪዎች 400,000 የ100,000 ብዜት ነው። ምክያቱም የ 400,000 በስተቀኝ የሚገኙ የመጨረሻው አምስት ሆሄዎች ሁሉም ዜሮ ናቸው። ተማሪዎች የ1,000 እና የ10,000 ብዜት የሆኑ ሙሉ ቁጥሮችን መደመር እናያለን ተማሪዎች የ1,000 እና የ10,000 ብዜቶችን የመደመር ውጤት ለማግኘት መጀመሪያ የሁለቱንም ድማሪዎች የመጨረሻ ሦስት ዜሮዎች መተውና የቀሩትን ሆሄያት መደመር ቀጥሎ ከውጤቱ በስተቀኝ ሦስት ዜሮዎችን በመፃፍ ድምሩ ይገኛል።
ምሳሌ1 ተማሪዎች 360,000 + 34,000 ደምሩ ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት? በጣም ጥሩ ተማሪዎች መጀመሪያ የሁለቱንም ድማሪዎች የመጨረሻ ሦስት ዜሮዎች በመተው 360ን እና 34ን መደመር ስለዚህ 360 + 34 = 394 ቀጥሎ ተማሪዎች ደምረን ያገኘነው ውጤት ላይ (394)ሦስት ዜሮች መጨመር 394,000 ማጠቃለያ ስለዚህ ተማሪዎች 360,000 + 34,000 = 394,000 ነው ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል ማለት ነው ።
ምሳሌ 2 ተማሪዎች 60,000 + 4000 ደምሩ ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት? በጣም ጥሩ ተማሪዎች መጀመሪያ የሁለቱንም ድማሪዎች የመጨረሻ ሦስት ዜሮዎች በመተው 60ን እና 4ን መደመር ስለዚህ 60 + 3 = 64 ቀጥሎ ተማሪዎች ደምረን ያገኘነው ውጤት ላይ (64)ሦስት ዜሮች መጨመር 63000 ማጠቃለያ ስለዚህ ተማሪዎች 60,000 + 4000 = 64000 ነው ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል ማለት ነው። ተማሪዎች አሁን ደግሞ የ100 ብዜት የሆኑ ሙሉ ቁጥሮችን መቀነስ እናያለን አንድ የ100 ብዜትን ከሌላ የ100 ብዜት ላይ ለመቀነስ ዋናው ከተቀናሹ ማነስ የለበትም።የመቀነስ ውጤት በመደመር ይረጋገጣል። የመደመር ውጤትም በመቀነስ ይረጋገጣል።
ምሳሌ 1 5600 – 3600 አስሉና መልሱን አረጋግጡ ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁት? በጣም ጥሩ ተማሪዎች ተማሪዎች የሁለቱም የ100 ብዜቶች ናቸው 5600 – 3600 = 2000 ነው አሁን ተማሪዎች የመቀነስ ውጤትን በ መደመር እናረጋግጣለን ሀ – ለ = መ ከሆነ ሀ = ለ + መ ነው ስለዚህ 3600 + 2000 = 5600 ነው ስለዚህ ትክክል ነው ማለት ነው ብላችሁ ከመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል ማለት ነው ።