ምዕራፍ 1 እንደምንአላችሁ ተማሪዎች
በ 2ኛ ክፍል ሒሳብ ትምህርት በምዕራፍ 1 ላይ
• ስለ እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮች መደመርና መቀነስ እንማራለን ስለ እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን ከተማርን በኃላ ሁላችሁም
* ከ 1 እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን እንከልሳለን
* ከ 1 እስከ 20 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን መደመርና መቀነስ እንከልሳለን
* ባለ አንድ አሃዝ ቁጥርን ከባለ ሁለት አሃዝ ቁጥር ጋር ያለ አለኝታና ያለብድር መደመርና መቀነስ ትችላላችሁ
* ባለ አንድ አሃዝ ቁጥርን ከባለ ሁለት አሃዝ ቁጥር በአለኝታ እና በብድር መደመርና መቀነስ ትችላላችሁ * ሁለት ባለ ሁለት አሃዝ ሙሉ ቁጥሮችን ያለ አለኝታ እና ያለ ብድር መደመር እና መቀነስ ትችላላችሁ * ሁለት ባለ ሁለት አሃዝ ሙሉ ቁጥሮችን በአለኝታ እና በብድር መደመር እና መቀነስ ትችላላችሁ * በመደመር እና በመቀነስ እስከ 100 ባሉ ሙሉ ቁጥሮች የሚሰሩ የቃላት ፕሮብሌሞችን ታውቃላችሁ 2ኛ ክፍል ሒሳብ ምዕራፍ 1
1.1 ከ እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን ክለሳ እንደምንአላችሁ ተማሪዎች
ዛሬ ደግሞ ከ 1 እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን እና ቅደም ተከተላቸውን ልንማር ተገናኝተናል
ዝግጁ ናችሁ ልጆች? • ተማሪዎች ስለ ከ 1 እስከ 100 ያሉ ሙሉ ቁጥሮች የተማራቹትን ታስታውሳላችሁ ካስታወሳቹ እስኪ ከታች ያሉትን ቁጥሮች ቁጠሩ
ልጆች ሁሉንም ቆጠራችሁ አይደል? ጎበዞች!
አሁን ደግሞ በሳጥኑ ውስጥ ያሉትን ምስሎች ብዛታቸውን ቁጠሩ
ልጆች ሁሉንም ሞከራችሁ አይደል? ጎበዞች! እስቲ አብረን እንቁጠር ልጆች? (1 2 3 4 5) ስለዚህ ተማሪዎች የመጀመሪያው ሳጥን ውስጥ 5 አፕሎች ነው ያሉት፡፡ እስቲ አብረን እንቁጠር ልጆች? ( 1 2 3)
ስለዚህ ተማሪዎች ሁለተኛው ሳጥን ውስጥ 3 ተማሪዎች ነው ያሉት።
እስቲ አብረን እንቁጠር ልጆች? ( 1 2 3 4 5 6)
ስለዚህ ተማሪዎች ሦስተኛው ሳጥን ውስጥ 6 አናናሶች ነው ያሉት። አሁን ደግሞ ነገሮችን መቁጠር እንማራለን፡ ዝግጁ ናችሁ ልጆች?
• ምሳሌ ቁጥር 1
ተማሪዎች፣ ተማሪ አበበ ስንት እግሮች አሉት?
እስቲ አብረን እንቁጠር ልጆች (1፣ 2)
ተማሪዎች ተማሪ አበበ 2 እግሮች አሉት ካላችሁ በትክክል መልሳችኋል። • ምሳሌ ቁጥር 2 ተማሪዎች፣ ተማሪ አበበ ስንት አይን አለው?
እስቲ አብረን እንቁጠር ልጆች (1፣ 2) ተማሪዎች ተማሪ አበበ 2 አይኖች አሉት ካላችሁ በትክክል መልሳችኋል። • ምሳሌ ቁጥር 3 ተማሪዎች፣ ተማሪ አበበ ስንት የእጅ ጣቶች አሉት?
እስቲ የግራ እጅ ጣቶቹን አብረን እንቁጠር ልጆች (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5) እስቲ የቀኝ እጅ ጣቶቹን አብረን እንቁጠር ልጆች (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5) እስቲ አሁን ደግሞ ሁለቱንም የእጅ ጣቶቹን አብረን እንቁጠር ልጆች (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10) ተማሪዎች ተማሪ አበበ 10 የእጅ ጣቶች አሉት ካላችሁ በትክክል መልሳችኋል። ተማሪዎች አሁን ደግሞ የጉደለውን ቁጥር በባዶ ቦታው ላይ እንሞላለን። ዝግጁ ናችሁ ልጆች?
• ምሳሌ ቁጥር 1
ተማሪዎች፣ ከ 10 ቀጥሎ የሚመጣው ሙሉ ቁጥር ____________ነው።
ተማሪዎች ይህንን ለማረጋገጥ እስቲ አብረን እንቁጠር፣
2፣ 4፣ 6፣ 8፣ 10 ካልን በኋላ 12 ነው የምንለው አይደል? ስለዚህ ከአስር (10) በኋላ የሚመጣው ሙሉ ቁጥር 12 ቁጥር ነው ማለት ነው፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 2
ተማሪዎች፣ ከ 5 ቀጥሎ የሚመጣው ሙሉ ቁጥር _____________ ነው።
ተማሪዎች እስቲ አብረን እንቁጠር፣
1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5 ካልን በኋላ 6 ነው የምንለው አይደል? ስለዚህ ከአምስት (5) በኋላ የሚመጣው ሙሉ ቁጥር 6 ቁጥር ነው ማለት ነው፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 3
ተማሪዎች፣ የ 99 ተከታይ ሙሉ ቁጥር ____________ ነው። ተማሪዎች እስቲ አብረን እንቁጠር፣
97፣ 98፣ 99 ካልን በኋላ 100 ነው የምንለው አይደል? ስለዚህ ከዘጠና ዘጠኝ (99) በኋላ የሚመጣው ሙሉ ቁጥር 100 ቁጥር ነው ማለት ነው፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 4
ተማሪዎች፣ የ 99 ቀዳማይ ______________ ነው። ተማሪዎች እስቲ አብረን እንቁጠር፣
100፣ 99፣ ካልን በኋላ 98 ነው የምንለው አይደል? ስለዚህ ከዘጠና ዘጠኝ (99) በፊት የለው ቁጥር 98 ቁጥር ነው ማለት ነው፡፡ ተማሪዎች አሁን ደግሞ ለተሰጡት ሙሉ ቁጥሮች ቀዳማይና ተከታይ እንፈልጋለን። ዝግጁ ናችሁ ልጆች? • ምሳሌ ቁጥር 1
ተማሪዎች፣ የ 21 ቀዳማይ _________ ሲሆን ተከታይ ___________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 20 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 22 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 2
ተማሪዎች፣ የ 18 ቀዳማይ ____________ ሲሆን ተከታይ ____________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 17 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 19 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 3
ተማሪዎች፣ የ 29 ቀዳማይ ____________ ሲሆን ተከታይ ____________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 28 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 30 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 4
ተማሪዎች፣ የ 25 ቀዳማይ ____________ ሲሆን ተከታይ ____________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 24 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 26 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 5
ተማሪዎች፣ የ 29 ቀዳማይ ____________ ሲሆን ተከታይ ____________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 28 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 30 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡ • ምሳሌ ቁጥር 6
ተማሪዎች፣ የ 99 ቀዳማይ ____________ ሲሆን ተከታይ ____________ ነው። ተማሪዎች ጥያቄውን ሞከራችሁ?
በጣም ጥሩ ተማሪዎች ቀዳማይ 98 ሲሆን ተከታይ ደግሞ 100 ብላችሁ የመለሳችሁ በትክክል መልሳችኋል፡፡